ደሴ: ግንቦት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 9ኛው የመላው አማራ ስፖርታዊ ጨዋታዎች የክብደት ማንሳት ውድድር በደሴ ከተማ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቅቋል። አራት ዞኖችን ያሳተፈው የክብደት ማንሳት ውድድር ላለፉት አራት ቀናት ሲያካሄድ ቆይቶ ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል።
ደሴ ከተማ ውድድሩን አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ 3 ወርቅ እና 2 ብር ሜዳሊያዎችን አሸንፏል።
ደቡብ ጎንደር እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር 1 ወርቅ 1 ብር እና 1 ነሃስ ሜዳሊያዎችን አግኝተዋል። ደቡብ ወሎ አንድ ብር እና አንድ ነሐስ በማግኘት ውድድሩን አጠናቅቋል።
ዘጋቢ: ኃይሉ አዳነ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን