ፒኤስጅ ፌራን ቶሬስን ማዘዋወሩን ይፋ አደረገ።

0
7

 

ፒኤስጅ ፌራን ቶሬስን ከባርሴሎና ማዘዋወሩን ይፋ አድርጓል።

የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጅ ለዝውውሩ 50 ሚሊዮን ዩሮ ከፍሏል። 5 ሚሊዮን እየታየ ጭማሪ ይኖረዋል ነው የተባለው። የ26 ዓመቱ አጥቂ እስከ 2031 የሚያቆየውን ውል ፈርሟል። 9 ቁጥር መለያ ይለብሳል።

ቶሬስ ከፊርማ በኋላ “ኢንርኬ ለእኔ በእግር ኳስ ሕይወቴ ውስጥ እንደ አባት ነው ” በማለት ለአሠልጣኙ ያለውን ክብር ገልጿል።

አሠልጣኙ የስፔን ብሔራዊ ቡድንን በሚመሩበት ወቅት እምነት ይጥሉበት እንደነበር እና በራስ መተማመኑን እንዳጎለበቱለት ተናግሯል።

አሠልጣኙ በበኩላቸው በፌራን ደስተኛ ነኝ፤ የፊት መስመራችንን አይበገሬ ያደርግልናል ብለዋል።
ፌራን በፒኤስጅ በግራ እና በቀኝ በዋና 9 ቁጥር እና ተደራቢ አጥቂ በመኾን ከአሠልጣኙ ፍልስፍና ጋር ተጣጥሞ ይጫወታል ተብሏል።

“ሻርኩ” በሚል ቅጽል የሚታወቀው ፌራን የዓለም እና የአውሮፓ ዋንጫን ጨምሮ በባርሴሎና እና በማንቸስተር ሲቲ ክለቦች 11 ዋንጫን አሳክቷል።

#አሚኮ #ስፖርት

#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_09_2018ዓ_ም

በንዋይ ሙሉጌታ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here