ማን ያሸንፋል?

0
59

አርሰናል ከ ማንቸስተር ሲቲ የሳምንቱ የሊጉ ታላቅ ጨዋታ!

ዛሬ ምሽት 1:30 በኢሚሬትስ ስታዲየም የፕሪሚየር ሊጉ 12ኛ ሳምንት ታላቁ ጨዋታ ይካሄዳል።

አርሰናል በ28 ነጥብ የሊጉ መሪ ሲኾን፣ ባለፉት 11 ጨዋታዎች ሽንፈት ሳይገጥመው ቀጥሏል። ብዙ ጨዋታዎችን በጠባብ ልዩነት ቢያሸንፍም፣ 7 ግቦች ብቻ ተቆጥረውበት በሊጉ ጠንካራ መከላከል ያለው ቡድን ነው።

ማንቸስተር ሲቲ በበኩሉ ቀደም ሲል ሊጉን መምራት ቢችልም ካለፉት 7 ጨዋታዎች 1ዱን ብቻ በማሸነፉ በ22 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ከዚህ ድክመት በመውጣት በሻምፒዮንነት ፉክክሩ ላይ ለመመለስ ዛሬ ይጫወታል።

የአርሰናሉ ሚኬል አርቴታ ከሲቲ ጋር የሚገኝ ውጤት ትልቅ ፋይዳ ቢኖረውም፣ ስለ ዋንጫ ለመናገር ጊዜው ገና ነው ብለዋል።

የማንቸስተር ሲቲው ኤንዞ ማሬስካ ያሉባቸውን ችግሮች በመለየት መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ ገልጸዋል። ኤርሊንግ ሃላንድ ባለፉት 4 ተከታታይ ጨዋታዎች ግብ አለማስቆጠሩም የቡድኑ ውጤት ማጣት ነፀብራቅ እንደኾነ አመልክተዋል።

ሌላው ተጠባቂው ጨዋታ 9:00 ኤቨርተን ከ ሊቨርፑል በመርሲ ሳይድ ደርቢ በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም የሚያደርገው ጨዋታ ነው።

ሊቨርፑል በ21 ነጥብ 4ኛ ሲኾን በ3 ጨዋታ 10 ግብ አስቆጥሮ 1 ተቆጥሮበታል፤ ኤቨርተን በዴቪድ ሞይስ እየሠለጠነ በ16 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በዕለቱ ሌሎች የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች 11:05 ላይ

ብራይተን ከ ኒውካስል

ክሪስታል ፓላስ ከ ሀል ሲቲ

ፉልሃም ከ ቦርንማውዝ

ሰንደርላንድ ከ ቶተንሃም ይጫዎታሉ

#አሚኮ #ስፖርት

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_20_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here