በ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር አየር ኀይሉን የማመሥገን ተግባር እየተካሄደ ነው።

0
31

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ያዘጋጀው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ “አየር ኀይላችን መመኪያችን” በሚል መሪ መልዕክት በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የአየር ኀይሉ 91ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ እየተካሄደ የሚገኘው የቢሾፍቱ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር የሕዝብና የሠራዊቱን ትሥሥር የሚያጠናክር መኾኑ ተገልጿል።

91 ዓመትን የዘለቀው አየር ኀይል የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር በየዘመናቱ ከፍተኛ መስዋትነትን የከፈሉ ጀግኖችም የሚታወሱበት ነው።

አየር ኃይሉ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተደረገው ሪፎርም በቴክኖሎጂ በመሠረተ ልማትና በሰው ኃይል አቅሙን እያሳደገ ይገኛል።

ይህም ለኢትዮጵያም ኾነ ለቀጣናው አስተማማኝ የአየር ኀይል ግንባታ ጉዞውን እያጎለበተ ነው።
#አሚኮ #ስፖርት

#አዲስ_አበባ #ኅዳር_20_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here