በ2025ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በሞሮኮ እና በሴኔጋል መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ተከትሎ የአህጉሪቱ ሻምፒዮን ማን እንደሚኾን የሚወስነው የዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (CAS) ነገ ማክሰኞ ኅዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም የመጨረሻ ውሳኔውን ይሰጣል።
ጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም በራባት በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ሴኔጋል በጭማሪ ሰዓት በፔፕጉዬ ብቸኛ ግብ ሞሮኮን 1 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አንስታ ነበር።
ኾኖም በጨዋታው መገባደጃ ላይ ለሞሮኮ የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት በመቃወም የሴኔጋል ተጫዋቾች ሜዳ ለቅቀው መውጣታቸውን ተከትሎ፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ሴኔጋል በፎርፌ እንደተሸነፈች በመቁጠር ሞሮኮን የ3 ለ 0 አሸናፊ እና የዋንጫው ባለቤት አድርጎ መወሰኑ ይታወሳል።
ፕላስ ጋና የተሰኘ የመገናኛ ብዙኀን እንዳስነበበው የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን የካፍን ውሳኔ በመቃወም በሜዳ ላይ ያገኘው ድል እንዲመለስለት ጉዳዩን ወደ የዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (CAS) የወሰደ ሲኾን፣ ሞሮኮ በበኩሏ በካፍ የተሰጣትን ዋንጫ ለማስጠበቅ ስትከራከር ቆይታለች።
ፍርድ ቤቱ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም በሎዛን የሁለቱንም ወገኖች ክርክር ካደመጠ በኋላ፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ቤተሰብ በጉጉት የሚጠብቀውን የመጨረሻ ብይን ነገ ይፋ ያደርጋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



