ጆዜ ሞሪንሆ ሪያል ማድሪድ በአቴንስ ከሚጠበቅበት የ2፡45ቱ አስቸጋሪ ጨዋታ በፊት ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል።
የሪያል ማድሪዱ አሠልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ቡድናቸው በሜዳው ጠንካራ ከሚባለው ተቃራኒ ቡድን ጋር በሚያደርገው የአውሮፓ ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረት እና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባውም ገልጸዋል።
አሠልጣኙ እንደተናገሩት ሪያል ማድሪድ በአቴንስ ባደረጋቸው 8 የአውሮፓ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ መኾኑን አስታውሰው፣ ይህም ጨዋታው ምን ያህል ከባድ እንደሚኾን ማሳያ ነው ብለዋል። ቡድናቸው ነጥብ የሚያስፈልገው በመኾኑ እና ምንም ዓይነት መዘናጋት ማሳየት ስለማይገባው፣ ያለውን ሙሉ አቅም ተጠቅሞ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና በለመደው የጨዋታ ደረጃ መጫወት እንዳለበት አሳስበዋል።
የኤኢኬ አቴንስ ዋና አሠልጣኝ ማርኮ ኒኮሊች ክለባቸው ባለፈው ዓመት ለኮንፈረንስ ሊግ ማለፉን እና የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱን በማስታወስ አሁንም በከፍተኛ ዕድገት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በሁለት ሳምንታት ልዩነት ውስጥ የደርቢ ጨዋታ እና ከሪል ማድሪድ ጋር የሚደረግን ግጥሚያ ማስተናገድ ፈታኝ መኾኑን የጠቆሙት አሠልጣኙ፣ ቡድናቸው በሜዳ ላይ የሚጠበቅበትን ምርጥ ብቃት ለማሳየት ዝግጁ መኾኑን አረጋግጠዋል።
የአርሰናሉ አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከስላቪያ ፕራግ 5፡00 ጨዋታ አስቀድሞ በሰጡት ሀሳብ አሠልጣኝ ጀንድሪች ትሮፒሶቮስኪ ጠንካራ አሠልጣኝ መኾናቸውን ገልጸው ጨዋታውን በልዩ ሁኔታ እንደሚያዩት ነው የተናገሩት።
አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከስላቪያ ፕራግ አሠልጣኝ ጋር ስላላቸው የጨዋታ ግንኙነት ሲናገሩ ተጋጣሚያቸው በአስር ዓመታት ቆይታቸው አስደናቂ ሥራ መሥራታቸውን ገልጸዋል። አርቴታ አሠልጣኙ በጨዋታ ስልት ብቻ ሳይኾን ተጫዎቾችን የሚይዙበት መንገድ፣ በክለቡ ባሕል እና በሥነ-ምግባር አርዓያ መኾናቸውን በማድነቅ ጨዋታው ቀላል እንዳልኾነ ነው የጠቆሙት።
ባለፈው የውድድር ዘመን የቡድኑ ፊት ለፊት ግንኙነትም ሁለት ጊዜ ቪዲዮውን በመመልከት እጅግ ጠንካራ እና በታላቅ ዲሲፕሊን የተዋቀረ ቡድን መኾኑን መገንዘባቸውን አውስተዋል።
የሲሊቪያ ፕራጋው አሠልጣኝ ጀንድሪች ትሮፒሶቮስኪ ከአርሰናል ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት በሰጡት አስተያየት ተፎካካሪያቸው ጠንካራ እና አነስተኛ የሜዳ ላይ ዕድል የሚሰጥ ቡድን መኾኑን ገልጸዋል።
አሠልጣኙ ቡድኑ በቅርቡ ከእንግሊዝ ሊግ ካፕ ቢሰናበትም በፍጥነት የማንሰራራት ብቃት እንዳለው ጠቁመው፣ ከቀደመው የውድድር ዘመን ተመሳሳይነት ያለው ቡድን ገንብቶ በምጣቱን ተናግረዋል።
ቡድናቸው የካርድ እና የፍጹም ቅጣት ምት ጥፋቶችን በመቀነስ እስከ መጨረሻው አቅሙ እንደሚታገልም አረጋግጠዋል።
በሌሎች ዛሬ በቻምፒዎንስ ሊግ በሚደረጉ ጨዋታዎች
👉ፌነርባቼ ከ ሊቨርፑል ምሽት 2፡45 ሲካሄድ
👉ቦርስያ ዶርትሙንድ ከ ሪያል ቤቲስ
👉ላንስ ከ ኮሞ
👉ፒኤስቪ ከ ክለብ ብሩጅ
👉ፖርቶ ከ ናፖሊ
👉አርቢ ሌፕዚግ ከ ማንቸስተር ሲቲ
👉ቪኪንግ ከ ሳባህ ኤፍኬ ምሽት 5፡00 የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_25_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



