ላሚን ያማል ትናንት ባርሴሎና አስቶን ቪላን በረታበት ጨዋታ አንድ ግብ አስቆጥሯል።
ይህች ግብም የባርሴሎናው ድንቅ ተጫዋች በኪሊያን ምባፔ ተይዞ የነበረውን የአውሮፓ ክብረወሰን እንዲያሻሽል ረድታለች።
ያማል በሻምፒዮንስ ሊግ ታሪክ ከ20 ዓመት በታች ሆኖ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋች መሆን ችሏል።
ክብረወሰኑ ከዚህ ቀደም በ13 ግቦች በኪሊያን ምባፔ ተይዞ የነበረ ሲሆን ትናንት ምሽት ያማል 14 በማድረስ ከፍ አድርጎታል።
ይህ ስፔናዊ ወጣት አጥቂ እነዚህን ግቦች ለማስቆጠር 37 የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ብቻ ነው የወሰደበት።
ቃልኪዳን ምስክር (የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምሕርት የተግባር ተለማማጅ)
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_25_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



