እንዳሰቡት መሆን ያቃታቸው ወጣቱ አሰልጣኝ!

0
42
በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከሳውዲው ክለብ አል አህሊ ኒውካስትል ዩናይትድን የተቀላቀሉት አሰልጣኝ ጃይሰል በነጭ እና ጥቁር ለባሾቹ ቤት የተጠበቀውን ያህል ውጤት ለማምጣት ተቸግረዋል።
በይበልጥ በአንድ ሳምንት ውስጥ በኤቨርተን ለሁለተኛ ጊዜ ሽንፈት ማስተናገዳቸው በኒውካስትል ቤት ያላቸው የስራ ዘመን እስከመች ይቆይ ይሆን የሚል ጥያቄ እያስነሳባቸው ይገኛል ።
በፕሪሚየር ሊጉ እስካሁን ከተደረጉ ጨዋታዎች ከፍተኛ የግብ ሙከራ ያስተናገዱት ኒውካስትሎች ናቸው።
ከተደረጉት ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ውስጥ በሰባቱ 15 እና ከዚያ በላይ የጎል ሙከራዎችን ያስተናገዱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ስህተት በመስራት አዲስ አዳጊዎቹ ሀል ሲቲ ከሰሩት 6 ስህተቶች በመቀጠል 5 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በመሳሳት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
በዚህም በፕሪሚየር ሊጉ በእድሜ ትንሹ ሁለተኛው አሰልጣኝ የሆኑት ጀርመናዊው አሰልጣኝ ቀሪ የስራ ዘመናቸውን ከባድ እንደሚሆንባቸው ይጠበቃል ።
ሰኞ እለት በተደረገው የ9 ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀግብር በሴንት ጀምስ ፓርክ ኤቨርተንን አስተናግደው በድጋሚ ሽንፈት የቀመሱት ኒውካስትሎች 17 የጎል ሙከራ ማድረግ ቢችሉም ኢላማውን የጠበቀው ሙከራ ማድረግ የቻሉት ግን ሁለት ጊዜ ብቻ ነው::
አሰልጣኝ ጀይሰል ከኤቨርተን ሽንፈት በኃላ ከደጋፊዎች ከፍተኛ የተቃውሞ ድምፅ የተሰነዘረባቸው ሲሆን ከጨዋታው በኃላ በሰጡት አስተያየትም በአሰልጣኝነት ዘመኔ እንደዚህ ያለ ሁኔታ ውስጥ ስገባ የመጀመሪያ ጊዜዬ አይደለም።
የደጋፊዎችን ቁጣም ሆነ ብስጭት እረዳለሁ። ለዚህም ተጠያቂው እኔ ነኝ ያለን ብቸኛ አማራጭ ግን በአንድነት መቆም እና አብሮ መስራት ነው በማለትም ተናግረዋል።
በክረምቱ የዝውውር መስኮት እንደ ብሩኖ ጉማሬሽ አንቶኒ ጎርደን እና ሳንድሮ ቶናሊን የመሳሰሉ ወሳኝ የክለቡን ተጨዋቾች የለቀቁት ነጭ እና ጥቁር ለባሾቹ ባለፉት ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች አራቱን ተሸንፈዋል።
በቀጣይ በፕሪሚየር ሊጉ ፉልሀምን ጨምሮ በደረጃ ሰንጠረዥ አንደኛ እና ሶሰተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኙት አርሰናል እና ብራይተን ሆቭ አልቢኦን ጋር ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን ካሉበት የ13ኛ ደረጃ ወደ ላይ ከፍ ይላሉ ውይስ ወደ ወራጅ ቀጠናው በይበልጥ ይጠጋሉ ከሚለው በይበልጥ ጀርመናዊው አሰልጣኝ በክለቡ ይቆያሉ ወይስ ይሰናበታሉ የሚለው ጉዳይ ይጠበቃል ።
ኤርምያስ ገረመው (የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምሕርት የተግባር ተለማማጅ)
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here