በ12 ኛ ሳምንት የሳውዲ ፕሮ ሊግ አልናስር ሜዳው ላይ አልኮሎድን ባስተናገደበት ጨዋታ 5 ለ 3 አሸንፏል::
በዚህ ጨዋታም ክርስቲያኖ ሮናልዶ 61፣ 72 እና 81ኛው ደቂቃ ላይ ጎሎችን አስቆጥሮ ሀትሪክ ሰርቷል::
ቀሪ የአልናስርን ጎሎች አንጌሎ እና ማኔ አስቆጥረዋል:: የአልኮሎድን ግቦች ደግሞ ዶሚኒጌዝ ሁለት ኢሶምባ አንድ አስቆጥረዋል::
የውድድር አመቱ የመጀመሪያ ሀትሪኩን የሰራው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ዘመኑ 68ኛ ሀትሪኩን ነው የሰራው:: የግብ መጠኑንም 985 ያደረሰ ሲኾን 1 ሽ ጎል ለመድረስ 15 ጎሎች ብቻ ይቀሩታል::
የ41 አመቱ ፖርችጋላዊ በትላንትናው እለት በደጋፊወች ምርጫ የምንጊዜም ምርጥ የባላንዶር አሸናፊ መባሉ ይታወሳል::
በቴዎድሮስ ኀ/ኢየሱስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



