በእንግሊዝ ሊግ ካፕ ጨዋታ ሲቲ ብራይተን ፤ሊቨርፑል ደግሞ ቸልሲን አሸንፈው ለሩብ ፍጻሜ ፍልሚያ ደርሰዋል።

0
79
ማንቸስተር ሲቲ በካራባኦ ካፕ ሩብ ፍጻሜ ማለፉን ያረጋገጠበት አስደናቂው የብራይተን ጨዋታ ይገኝበታል። በምሽቱ የሁለቱ ክለቦች መካከል በተደረገው ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ ጨዋታውን በመቆጣጠር ረገድ የላቀ ድርሻ ነበረው ቢኾንም ብራይተኖችም ያልተናነሰ ትግል ነው ያደረጉት።
ውሀ ሰማያዊዎቹ 56 በመቶ የኳስ ቁጥጥር የነበራቸው ሲኾን፣ በተሻለ እና በተሳኩ የኳስ ቅብብሎሽም ጥሩ የሚባሉ ነበሩ።
በአንጻሩ ብራይተኖችም 44 በመቶ የኳስ ቁጥጥር እና የተሻለ የኳስ ቅብብሎሽን በማድረግ ጨዋታው ለተመልካች ማራኪ እና ተመጣጣኝ እንዲኾን አስችለውታል።
ጨዋታው በመደበኛ ጊዜ 2ለ2 ተጠናቋል። ለሲቲ ግቦቹን ኮቨችች ከእረፍት በፊት እና ቪክቶር ሪስ ከእረፍት መልስ አስቆጥረዋል። ለብራይተን ደግሞ ከእረፍት በፊት ቫልኮይ እና ሩተር ኳሶችን ከመረብ አሳርፈዋል።
መደበኛው ሰዓት በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ የመለያ የፍጹም ቅጣት ምት ተሰጧል። ማንቸስተር ሲቲ 4ለ3 በኾነ ውጤት አሸንፎ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
ሌላው የምሽቱ ማራኪ እና ጠንካራ ፉክክር የታየበት የሊቨርፑል እና የቼልሲ ጨዋታ ይገኝበታል።
በመደበኛው ክፍለ ጊዜ ጨዋታው 1ለ1 ሲጠናቀቅ ለሊቨርፑል ከእረፍት በፊት ጋግፖ ለቸልሲ ደግሞ ሞርጋን ሮጀርስ ግቦችን አስቆጥሯል።
ጨዋታውም ወደ ፍጹም ቅጣት ምት አምርቶ ሊቨርፑል 6ለ5 በኾነ ውጤት ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
በሌላ የምሽቱ ጨዋታ ቦርንማውዝ አስቶን ቪላን 3ለ0፤ ክርስታል ፓላስ ፉልሀምን 1ለ0 እና ሰንደርላንድ ብሬንት ፎርድን 3ለ2 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀል ችለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here