በሴሪ ኤ የደመቀዉ ዶናይል ማለን

0
69
ኔዘርላንዳዊው አጥቂ ዶናይል ማለን ወደ ጣሊያኑ ኤኤስ ሮማ ካመራ በኋላ ድንቅ ብቃቱን መልሶ በማግኘት ላይ ይገኛል።
በአስቶን ቪላ እና ቦሩሲያ ዶርትመንድ በነበረው ቆይታ መደበኛ የመሰለፍ ዕድል ለማግኘትና ብቃቱን ለማውጣት ተቸግሮ የነበረው ማለን፣ በሮማ ቤት ግን የፊት መስመሩ ቁልፍ ሰው መሆን ችሏል።
ባለፈዉ አመት በውሰት ከአስቶንቪላ ወደ ሮማ በማምራት በግማሽ የውድድር ዘመን ብቻ 14 የሴሪ ኤ ግቦችን በማስቆጠር የሮማ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ማጠናቀቅ ችሏል።
በዚህም ሮማ ከ7 ዓመታት በኋላ ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ እንዲመለስ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። በተጨዋቹ ብቃት የተደሰተዉ ሮማ በ25 ሚሊዮን እስከ 2030 በሚያቆየው ውል አስፈርሞታል።
ማለን በዘንድሮዉ የሴሪ ኤ ዘጠኝ ሳምንት ጨዋታዎች 7 ግቦችን ከመረብ አገናኝቶ የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን እየመራ ነዉ፡፡
ዶናይል ማለን በአስቶን ቪላ በነበረው የሁለት የውድድር ዘመናት ቆይታ በሁሉም ውድድሮች በአጠቃላይ 46 ጨዋታዎችን አድርጎ 10 ግቦችን ብቻ ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡
ከአጥቂዎች ተፈጥሯዊ ተክለ ሰዉነት ባህሪ ጋር ሲነፃፀር አጭር የሆነዉ ዶናይል ማለን፤ ተጫዋቹ ያለዉ ፍጥነት እና ግብ የማግባት ክህሎቱ በጣሊያን ሴሪ ኤ ደምቆ እንዲወጣና በሮማ ደጋፊዎች ዘንድ ተወዳጅነትን እንዲያገኝ አድርጎታል።
በአንጋፋዉ አሰልጣኝ ጂያን ፒዬሮ ጋስፔሪኒ የሚሰለጥነዉ የዋና ከተማዋ ክለብ ሮማም በሴሪ ኤ ያለሽንፈት እየተጓዘ ሲሆን በ21 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
በታሪኩ ዐይኔዋ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here