ታሪክ
በ1956 እ.ኤ.አ. ፈረንሳይ ፉትቦል በተሰኘው የፈረንሳይ መጽሔት በሁለት የስፖርት ጸሐፊዎች የተመሰረተው ባሎንዶር በዓለም እግር ኳስ ውስጥ ለምርጥ ወንድ እና ሴት ተጫዋቾች የሚሰጥ ሽልማት ነው።
ፈረንሳይ ፉትቦል የሽልማቱ እና የድምፅ አሰጣጡ አዘጋጅ ሆኖ የቀጠለ ቢሆንም የስነ-ስርዓቱ ዝግጅት ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ጋር በጋራ የሚዘጋጅ ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ፣ ሽልማቱ የተፈጠረው አውሮፓዊ ምርጥ ወንድ ተጫዋች ለመሸለም ነበር። በ1995 እ.ኤ.አ. በአህጉሪቱ የሚጫወቱ አውሮፓውያን ያልሆኑ ተጫዋቾችን እንዲያካትት ከተደረገ በኋላ በ2007 እ.ኤ.አ. ደግሞ ዓለም አቀፋዊ ሽልማት ለመሆን በቅቷል።
የሴቶች ባሎንዶር ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀው በ2018 እ.ኤ.አ. ሲሆን በወቅቱ ለሊዮን ትጫወት የነበረችው አዳ ሄገርበርግ የመክፈቻው ዓመት አሸናፊ ነበረች።
የዘንድሮው ባላንዶር ሽልማት የዚህ ዓመት የሽልማት ስነ-ስርዓት የባሎንዶርን 70ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በማስመልከት የመጀመሪያ ዓመት አሸናፊ ለነበሩት ለእንግሊዙ ስታንሊ ማቲውስ እውቅና ለመስጠት ሲባል በለንደን ይካሄዳል። ቦታው ሶሆ በሚገኘው የለንደን ፓላዲየም ቲያትር ሲሆን መርሀግብሩ እለተ ሰኞ ምሽት 4:00 ሰዓት ይጀምራል።
የ2026 የባሎንዶር አሸናፊነት ቅድመ ግምት የተሰጣቸው እነማን ናቸው?
የባርሴሎና እና የስፔን ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ላሚን ያማል፣ የሪያል ማድሪዱ ፈረንሳዊው ክሊያን ምባፔ እና እንግሊዛዊው የባየር ሙኒክ አጥቂ ሀሪ ኬን ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው ተጫዋቾች ናቸው::
በሴቶች ደግሞ የለንደን ሲቲዋ እና የስፔን ኮከብ አሌክሲያ ፑቴላስ ለሴቶች ባሎንዶር ቅድመ ግምት የተሰጣት ሲሆን የቀድሞ የባርሴሎና የቡድን አጋሮቿ ኢዋ ፓጆር እና ያለፈው ዓመት አሸናፊዋ አይታና ቦንማቲ ሁነኛ ተፎካካሪወቿ ናቸው ።
የድምፅ አሰጣጥ መስፈርቱ ምንድን ነው?
ተጫዋቾቹ የሚገመገሙት ከነሐሴ 3 ቀን 2025 እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2026 ባለው የባለፈው የውድድር ዘመን ባሳዩት ብቃት ነው።
የባሎንዶር አሸናፊዎች በአስፈላጊነታቸው ቅደም ተከተል መሠረት በሦስት ዋና ዋና መስፈርቶች ይገመገማሉ እነርሱም የግል ብቃት፣ የቡድን ብቃት እና ያሸነፏቸው ዋንጫዎች እንዲሁም ስፖርታዊ ጨዋነት ናቸው ።
ባላንዶርን ደጋግመው ያነሱ ተጫዋቾች
እለተ ሰኞ ጥቅምት 16 ምሽት በሎንደን በሚደረገው የባላንዶር ሽልማት መርሀግብር የአለም የእግርኳስ ከዋከብቶች ይታደሙበታል:: በታሪክ ደጋግሞ ባላንዶርን በማሸነፍ ሊዮኒል ሜሲ ስምንት ጊዜ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ደግሞ አምስት ጊዜ በመውሰድ ታሪካዊ ተጨዋቾች ናቸው::
ሚሼል ፕላቲኒ፣ ዩዋን ክራይፍ እና ማርኮ ቫንባስተን ባላንዶርን ለተከታታይ ሶስት ጊዜ ማሸነፍ የቻሉ ተጫዋቾች ናቸው::
ድምጽ የሚሰጡ እነማን ናቸው?
የባልንዶርን ድምጽ የሚሰጡ በፉፋ ደረጃ እስከ 100ኛ ያሉ ሀገራት የተወከሉ አንድ አንድ ጋዜጠኞች ሲሆኑ በፍራንስ ፉትቦል አዘጋጅነት ለእያንዳንዳቸው አስር አስር ስም ዝርዝር ይሰጣቸውና ድምጻቸውን በደረጃ ያስቀምጥሉ::ነጥቡም ከ15 እስከ 1 የሚያዝ ነው::
ያለፈው አመት አሸናፊወች
በወንዶች ፈርንሳያዊው ኦስማን ዴምቤሌ ሲኾን በሴቶች ደግሞ ስፔናዊቷ አይታና ቦንማቲ ናቸው::
በዘንድሮ ሽልማት ምን አዲስ?
በዘንድሮው የባላንዶር ሽልማት ደግሞ የምንጊዜም የባላንዶር አሸናፊ (BOAT) ይመረጣል::በዚህ ዝርዝር ውስጥ 10 እጮወች የተካተቱ ሲሆን በደጋፊወች ምርጫ አሸናፊው ይለያል::
በምንጊዜም ምርጥ የባላንዶር አሸናፊ ሜሲ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ሮናልዶ ሊዩስ ናዛሪዮ ዴሌማ፣ ሚሼል ፕላቲኒ፣ ማርኮ ቫንባስተን፣ ዩዋን ክራይፍ፣ ኬቨን ኬጋን፣ ሄንዝ ሩሚንጌ፣ ፍራንዝ ቤከንባወር እና አልፌርዶ ዲ ስቴፋኖ ይገኙበታል::
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



