ዛሬ ሁለት ጠንካራ ክለቦችን የሚያገናኘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬም ቀጥሎ ይካሄዳል።

0
22

 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 1ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም ሲቀጥሉ በሀላባ ስቴዲየም ወላይታ ዲቻ ከፋሲል ከነማ ይጫወታሉ።

አፄዎቹ በውድድር ዓመቱ ጠንካራ ተፎካካሪ ለመኾን በተጫዋቾች ዝውውር ላይ በንቃት በመሳተፍ ሥብሥባቸውን አጠናክረዋል። የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውንም በአዳማ ከተማ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

አራት የወዳጅነት ጨዋታዎችን አድርገው ሁለቱን ሲያሸንፉ በሁለቱ አቻ ተለያይተው ወደ ሀላባ አቅንተዋል።

ተጋጣሚያቸው ወላይታ ዲቻ በበኩሉ በቅድመ ዝግጅት ጊዜያቸው ከሀዋሳ ከተማ ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን አድርገው ሁለቱንም ያሸነፉ ሲኾን በኢትዮጵያ ቡና ተሸንፈዋል።

ነባር እና አዳዲስ ተጫዋቾችን የያዘው የአሠልጣኝ መሳይ ተፈሪ ሥብሥብ ዛሬ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ከፋሲል ከነማ ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ የውድድር ዓመቱን ይጀምራል።

ከዚህ ጨዋታ ቀድሞ በአዲስ አበባ ስቴዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከነጌሌ አርሲ ከሰዓት በኋላ 9:00 ላይ ይጫወታሉ።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_30_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ዳናይት ሲሳይ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here