ኮል ፓልመር ከቼልሲ ጋር እስከ 2034 የሚቆይ አዲስ የረጅም ጊዜ ውል ተፈራረመ

0
20

 

የእንግሊዙ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ ቼልሲ ድንቁ አማካይ ኮል ፓልመር ከክለቡ ጋር ያደረገውን ኮንትራት እስከ 2034 የሚያቆየውን አዲስ እና የተሻሻለ የረጅም ጊዜ ውል በይፋ መፈረሙን አረጋግጧል።

በምዕራብ ለንደኑ ክለብ በረጅም ጊዜ የዝውውር ስትራቴጂያቸው ከሚታወቁት አንዱ ሲኾን ከዚህ ቀደም እንደ ሪስ ጄምስ፣ ሞይሰስ ካይሴዶ እና ፔድሮ ኔቶ ያሉ ቁልፍ ተጫዋቾች ውላቸውን ማራዘማቸው ይታወሳል።

ውሉን ከፈረመ በኋላ ኮል ፓልመር በሰጠው አስተያየት «አሁን ቼልሲ ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ እየተጓዘ እንደኾነ አምናለሁ፤ ይህንን ውል በመፈረሜ እጅግ ደስተኛ ነኝ» ብሏል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_30_2019_ዓ_ም

በዳናይት ሲሳይ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here