በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ተወካዩ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በድሬዳዋ ስታዲየም የሱዳኑን ሂላል አል ሳሕል ያስተናግዳል።
በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአህጉራዊ መድረክ እየተሳተፈ የሚገኘው ወልዋሎ ዓዲግራት ከሳምንት በፊት በሩዋንዳ ኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ 2 ለ 1 በኾነ ውጤት መረታቱ ይታወሳል። ኾኖም ቢጫ ለባሾቹ በአማካዩ ካርሎስ ዳምጠው አማካኝነት ያገኟት ከሜዳ ውጭ ውድ ግብ ለዛሬው የመልስ ፍልሚያ ጥሩ የሥነ-ልቦና የበላይነት ሰጥታቸዋለች።
ወልዋሎ ዓዲግራት ወደ ሁለተኛው ዙር ማለፉን ለማረጋገጥ በዛሬው ጨዋታ 1 ለ 0 በማሸነፍ በከሜዳ ውጭ ግብ ሕግ አልያም በሁለት ግብ ልዩነት የበላይነትን መውሰድ ይጠበቅበታል።
ይህ ተጠባቂ አህጉራዊ ጨዋታ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በድሬዳዋ ስታዲየም የሚከናወን ይኾናል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
ባሕር ዳር #መስከረም_02/2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



