ባለፈው ዓመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለጥቂት ከመውረድ የተረፈው ቶተናም የዘንድሮ አጀማመሩም ጥሩ አይመስልም።
ገና በመጀመሪያው ሳምንት መርሀ ግብር ከሜዳው ውጭ በብሬንትፎርድ 3 ለ 0 በኾነ ሰፊ ውጤት ተሸንፏል።
ይህ መጥፎ አጀማመር ያስደነገጣቸው አዲሱ የቶተናም አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ፈጣን የተጫዋቾች ዝውውር እያካሄዱ ነው።
በዛሬው ዕለት ሳቪንሆን በ75 ሚሊዮን ፓውንድ ከማንቸስተር ሲቲ ያስፈረመው ቶተናም አሁን ደግሞ ሌላውን የሲቲ ተጫዋች ኦማር ማርሙሽን ለማስፈረም መስማማቱ ተነግሯል።
ታዋቂውን ዓለም አቀፍ የተጫዋቾች ወኪል ፋብሪዚዮ ሮማኖን ጠቅሶ ያሁ ስፖርትስ እንደዘገበው ቶተናም ግብፃዊውን አጥቂ በ60 ሚሊዮን ፓውንድ ለመውሰድ ተስማምቷል።
ዝውውሩም በጥቂት ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ሀይሌ አበራ



