ጋና፣ ፈረንሳይ፣ ኖርዌይ፣ ኬፕቨርዴ፣ ስፔን፣ ፖርቱጋል እና እንግሊዝ ወደ ጥሎ ማለፉ ተቀላቀሉ።

0
69

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ ዘጠኝ የመጨረሻ ጨዋታ ሴኔጋል ኢራቅን 5 ለ 0 በኾነ ውጤት አሸንፋለች። ይህ ድል ሴኔጋል የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎችን ከተሸነፉ በኋላ ያገኙት ወሳኝ የ3 ነጥብ እና በግብ ክፍያ ማሻሻያ ከምድባቸው 3ኛ ደረጃን ይዘው ከሚያጠናቅቁት 8 ምርጥ ቡድኖች መካከል አንዱ በመኾን ወደ 32ቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የመግባት ዕድሏን በእጅጉ አስፍቶላታል።

በዚህ ሽንፈት ምክንያት ሦሥቱንም የምድብ ጨዋታዎች የተሸነፈችው ኢራቅ ከውድድሩ ውጭ መኾኗ ተረጋግጧል። ሴኔጋል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን ለማወቅ የሌሎች ምድቦችን ጨዋታዎች ውጤት ትጠብቃለች።

ፈረንሳይ ኖርዌይን 4ለ1 በኾነ ውጤት በማሸነፍ ምድቡን በመምራት ወደ ቀጣዩ ዙር ተሸጋግራለች።

ኡስማን ዴምቤሌ በጨዋታው ሦሥት ግብ በማስቆጠር ሀትሪክ ሠርቷል። ይህም በዓለም ዋንጫ ታሪክ ሁለተኛው ፈጣን ሀትሪክ ኾኖ ተመዝግቧል። ዴዚሬ ዱዌ አራተኛዋን ግብ አስቆጥሯል። በዚህ ውጤት መሠረትም በቀጣይ ከስዊድን ጋር የምትገናኝ ይኾናል። ኖርዌይም በሁለተኛነት ከምድቡ ማለፏን አረጋግጣለች።

በኳስ አፍቃሪያን ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን እያተረፉ የሚገኙት ኬፕቨርዴዎች አስደናቂ ተጋድሎ በማድረግ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ይህ ስኬት ደሴቲቱ ሀገር በዓለም ዋንጫ ታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የምድብ ማጣሪያውን አልፋ ወደ ቀጣዩ ደረጃ የተሻገረችበት ታሪካዊ ክስተት ኾኖ ተመዝግቧል።

ስፔን ኡራጓይን 1 ለ 0 በኾነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ ምድቡን በአንደኝነት አጠናቃ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች።

በሌላኛው የምድብ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ከሳውዲ አረቢያ ጋር 0 ለ 0 በኾነ ውጤት በመለያየቷ ኡራጓይን በጎል ልዩነት በልጣ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ቀጣዩ ዙር በማለፏ ሳቢያ ባለ ሁለት ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ኡራጓይ ከምድቡ በለቅሶ ተሰናብታለች።

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የሚመራት ፖርቱጋልም ማለፏን አረጋግጣለች።

እንግሊዝ እያሳየች ባለው ጠንካራ ብቃት በመታገዝ ከምድብ ጨዋታዎች አስደናቂ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች።

እንግሊዝ፣ ክሮኤሺያ እና ፓናማ ባሉበት ምድብ ያለችው ጋና ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች።

በሌላ የንጋት ጨዋታዎች ግብጽ እና ፖራጓይም ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here