የታላላቅ ክለቦች የተጫዋች ፍለጋ !

0
44

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ እግር ኳስ የክረምት የዝውውር ወቅት ሊጀምር ጥቂት ጊዜ ቀርቶታል።

በአሁኑ ወቅት ታላላቅ ክለቦች ሥብሥባቸውን ለማጠናከር እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ።

ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ የቦርንማውዙን የ22 ዓመቱን አማካኝ አሌክስ ስኮትን በክረምቱ የዝውውር ወቅት ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል። ኾኖም ቦርንማውዝ አሌክስ ስኮትን የመሸጥ ፍላጎት እንዴለው ስካይ ስፖርት አስነብቧል።

የማንቸስተር ሲቲ እና የፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ የኾነው የ29 ዓመቱ ሮበን ዲያስ ከክለቡ ለመልቀቅ እንዲያመቻቹለት ለወኪሉ ተናግሯል ተብሏል። ተጫዋቹን ለማስፈረም ፒ ኤስ ጂ፣ ባየር ሙኒክ እና ሪያል ማድሪድ ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተሉ እንደሚገኙ ያስነበበው ደግሞ ዴይሊ ሜል ነው።

ሊቨርፑል የ19 ዓመቱን የአርቢ ላይፕዚግ እና የኮትዲቯር የክንፍ ተጫዋቹን ያን ዲዮማንዴን ለማስፈረም ጥረት እያደረገ ነው። ፒ ኤስ ጂ እና ማንቸስተር ሲቲም ተጫዋቹን በቅርብ እየተከታተሉት መኾናቸውን ዘጋርዲያን ዘግቧል።

ማንቸስተር ሲቲ በቶተንሃም የሚፈለገው ብራዚላዊ የክንፍ ተጫዋች ሳቪንሆ ክለቡን ለቆ የሚሄድ ከኾነ ሊተካው የሚችለውን አማራጭ እያጠና ነው ሲል ፉትቦል ኢንሳይደር ገልጿል።

ባርሴሎና የ24 ዓመቱን የአርሰናል እና የኢኳዶር ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ፒዬሮ ሂንካፒን ለማስፈረም አማራጮችን እያሰላሰለ ይገኛል ተብሏል።

ክሪስታል ፓላስ የኮንፈረንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፉን ተከትሎ የ22 ዓመቱን እንግሊዛዊ አማካኝ አዳም ዋርተን እና የ29 ዓመቱን ጃፓናዊ አማካኝ ዳይቺ ካማዳን በክለቡ እንዲቆዩ እየሠራ መኾኑ ተገልጿል።

ስፖርቲንግ ሊዝበን በቶተንሃም በውሰት የሚገኘውን የ30 ዓመቱን የባየር ሙኒክ አማካኝ ጆአዎ ፓልኒሃ የውሰት ውሉ ሲያልቅ መልሶ በቋሚነት ለማስፈረም ይፈልጋል ተብሏል።

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት_ጭምጭምታ #እግር_ኳስ

በምስጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here