🇪🇹 ኢትዮጵያ ከሞዛምቢክ ጋር ዛሬ ወሳኙን የመለያ ጨዋታ ታደርጋለች።

0
57

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከ22 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ መድረክ መመለስ የቻለው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ወደ ዓለም ዋንጫ ለማለፍ የመለያ ጨዋታውን ዛሬ ከሞዛምቢክ ጋር ያደርጋል።

ብሔራዊ ቡድኑ ቱኒዚያን በማሸነፍ ከምድብ “ሀ” ሦሥተኛ ኾኖ ማጠናቀቁ የሚታወስ ሲኾን በውድድሩ ደንብ መሠረት የመለያ ጨዋታ ምድብ “ሐ” ላይ 3ኛ ደረጃ ይዞ ካጠናቀቀው ሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን ጋር ነው ዛሬ የሚጫወተው።

ብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታውን ማሸነፍ ከቻለም በኳታር አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የ2026 ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ የሚያልፍ ይኾናል።

በአሠልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዛሬውን ወሳኝ ጨዋታ አሸንፎ ለመውጣት ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርግ ነው የሚጠበቀው።

ብሔራዊ ቡድኑ ለዚህ ወሳኝ ውድድር ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ መኾኑን የኢትዮጵያ ፉት ቦል ፌዴሬሽን በማኅበራዊ የትስስር ገጹ አስፍሯል።

ተጫዋቾቹም ምሽት 1፡00 ላይ ለሚካሄደው ጨዋታ ውጤታማ ለመኾን ዝግጁ መኾናቸው ተመላክቷል።

በምስጋናው ብርሃኔ

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here