ባሕር ዳር: ግንቦት 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ከእነዚህ ጨዋታዎች መካከል ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ቀን 9፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፈው ክለብ ደረጃውን ያሻሽላል።
በሌላ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከድሬዳዋ ከተማ ምሽት 12፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ሸገር ከተማ ከመቀለ 70 እንደርታ ቀን 7፡00 ሲጫወቱ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀዋሳ ከተማ ቀን 10፡00 ላይ በአዲስ አበባ አበበ ቢቄላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በምስጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !



