የ”ኢትዮጵያ ታምርት” የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሄደ።

0
42

 

አዲስ አበባ: ሚያዝያ 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ንቅናቄን ለማስተዋወቅ የታለመው የ”ኢትዮጵያ ታምርት” የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በውድድሩ ላይ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የተጀመረው የ”ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ የገቢ ምርትን በመተካት ረገድ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መኾኑን ገልጸዋል። ሚኒስትሩ አክለውም መንግሥት ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሰጠው ትኩረት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ውድድሩ ለአትሌቶች የውድድር ዕድል ከመፍጠሩ ባለፈ የዘርፉን ችግሮች ለመፍታት እና ንቅናቄውን ለማኅበረሰቡ ለማስተዋወቅ ትልቅ ሚና እንዳለው ተመላክቷል። ከአትሌቶቹ ውድድር በተጨማሪ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሕዝባዊ ሩጫም ተካሂዷል።

500 ገደማ አትሌቶች በተሳተፉበት በዚህ ውድድር ንብረት ክንዴ በወንዶች፣ ብርቱካን ሞላ ደግሞ በሴቶች አሸናፊ በመኾን የ550 ሺህ ብር ሽልማት ባለቤት ኾነዋል።

በውድድሩም በወንዶች፦ 1ኛ ንብረት ክንዴ (ንግድ ባንክ)፣ 2ኛ ጀምበሩ ሲሳይ (በግል)፣ 3ኛ ግዛቸው ሙሴ (ንግድ ባንክ)።

በሴቶች፦ 1ኛ ብርቱካን ሞላ (በግል)፣ 2ኛ ሮቤ ዲዳ (ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን)፣ 3ኛ ኑሪት አህመድ (ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን)ኾነው አጠናቅቀዋል።

ዘጋቢ፦ ባዘዘው መኮንን

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here