ፈተናዎችን ያለፈው ስኬት!

1

ኢትዮጵያ በታሪክ ሂደቷ ውስጥ ከውጭ ኀይሎች በተለይም ከግብጽ እና ከስልታዊ አጋሮቿ በሚሰነዘር የግፍ ሴራ በርካታ ፈተናዎችን ስትቋቋም ቆይታለች።

የኢኮኖሚ ዕድገቷን ለመገደብ፣ የውኃ ሀብቷን እንዳትጠቀም እና የባሕር በር ባለቤትነቷን እንድታጣ በማድረግ የጂኦ ፖለቲካዊ አቅሟን ለማዳከም የካይሮ መንግሥት ለዘመናት ሠርቷል።

በጉንደት ጦርነት እ.ኤ.አ በ1875 ግብጽ በሰሜን ኢትዮጵያ ወረራ ማድረጓን የታሪክ መጽሐፍት ያስረዳሉ። እ.ኤ.አ በ1876 በጉራ ጦርነት ግብጽ ዳግመኛ ወረራ አካሂዳም ነበር።

በሁለቱም የወረራ ሙከራዎች በኢትዮጵያውያን ጀግኖች የማይረሳ ሸንፈትን ተከናንባ መመለሷን የታሪክ ድርሳናት መዝግበዋል።

​ግብጽ የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊ መብት ለመቀማት ከብሪታንያ ቅኝ ግዛት አሥተዳደር ጋር በመተባበር የዘመናት ግፍ ፈጽማለች።

​የ1929 እና የ1959 ስምምነቶች የናይል ውኃ ከ85 በመቶ በላይ የሚመነጨው ከኢትዮጵያ (ከዓባይ) ቢኾንም ግብጽ እና ሱዳን ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ በማግለል የዓባይን ውኃ ለራሳቸው ብቻ የሚከፋፍል አፋኝ ስምምነት መፈራረማቸውን ታሪክ ያስረዳል።

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የውኃ ማከማቻ፣ የግብርና ልማት፣ የኀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ለመሥራት በሞከረች ቁጥር ግብጽ ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት እና ከሌሎች አካላት ብድር እንዳታገኝ ዘብ ቆማ ሠርታለች።

የኢትዮጵያ ታሪክ ሲገለጥ በቀይ ባሕር እና በዓባይ ሸለቆ መሠረቱን የጣለ መኾኑን ፕሮፌሰር ላጵሶ ጌ ድሌቦ” የኢትዮጵያ ታሪካዊ መሠረቶች እና መሣሪያዎች” በተሰኘው መጽሐፍቸው አስቀምጠዋል።

መነሻውን ከኢትዮጵያ ምድር ያደረገውን የዓባይ ወንዝን ለዘመናት እየተጠቀመች የምትገኘው ግብጽ የሕዳሴ ግድብ እንዳይገነባ ጥረት አድርጋለች። ግድቡም ተጠናቅቆ በቂ ውኃን እየተጠቀመች የምትገኘው ግብጽ ግን ኢትዮጵያ የባሕር በር ተጠቃሚ እንዳትኾን እየሠራች ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሰሞኑ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢትዮጵያ የባህር በር መብቷን በሰላም እና በንግግር መፍታት ነው የምትፈልገው ነው ያሉት።

ዓባይ ከጣና ቢነሳም በተፈጥሮ መንገድ ሱዳን እንደሚገባ ነገር ግን ዓባይን ሱዳን አትገባም ብለን ብንገድበው እኛን ይዞ ይሄዳል እንጅ አናቆመውም፣ የቀይ ባሕርም ጉዳይ ልክ እንደዚሁ እንደኾነ የኤርትራ መንግሥት ሊያውቅ ይገባል ነው ያሉት።

ሰጥቶ በመቀበል መርሕ የባሕር በር ማግኘት ነው የምንፈልግ ነው ያሉት። በምድርም በሰማይም ተዘግተን ሰላም የሚኾን ቀጣና ብሎም ሰላም የሚኾን አፍሪካ ሕልም ነው ብለዋል። እነሱም እኛም እንጠቀም በጋራ እንደግ ነው ያሉት።

✍️ ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_19_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleኢትዮጵያ ትጋቷን እና ታላቅነቷን የምትገልጥበት እድል