ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ይካሄዳል።

31

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች እና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 በጀት ዓመት የመንግሥት ዕቅድ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩም በወቅቱ ፕሬዚዳንት ታዬ ያቀረቡትን የመንግሥት ዕቅድ መነሻ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መንግሥት በቀጣይ ትኩረት የሚያደርግባቸውን አቅጣጫዎች በግልጽ እንደሚያስቀምጡም ይጠበቃል፡፡

በአዲሱ በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ሥራዎችን እና የተገኙ ውጤቶችንም ያብራራሉ፡፡

ምክር ቤቱ የመንግሥትን አቋም ካዳመጠ በኋላ ፕሬዚዳንት ታዬ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

በጉባኤው በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በክብር እንግድነት ይታደማሉ፡፡

አሚኮ በሁሉም የሥርጭት አማራጮች ጉባኤው በቀጥታ ሥርጭት እንደሚያስተላልፍ እየገለጽን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።

‎#የመደመር_መንግሥት!

‎

‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

‎‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_17_2019_ዓ_ም

‎‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ነገ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ ይሰጣሉ።
Next articleየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው።