የአዲስ አበባ ሰው ተኮር ልማቶች ማኅበራዊ እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ ነው።

0

የሰው ተኮር የልማት ሥራዎች የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻል ባለፈ፣ ማኅበራዊ፣ ፍትሐዊ እና ሁሉን ያካተተ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና አላቸው። የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ የተገነቡ የሰው ተኮር የልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጥሩማር አባተ የተሳተፉ ሲኾን በከተማዋ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን እናቶች፣ ሕጻናት እና አረጋውያንን ተጠቃሚ ለማድረግ የተተገበሩ የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።

ከተጎበኙት የልማት ሥራዎች መካከል በእንጦጦ የተገነባው የእናቶች የእንጀራ መጋገሪያ የተቀናጀ የልማት መንደር ይገኝበታል። መንደሩ ቀደም ሲል በእንጨት ለቀማ ሥራ ቤተሰቦቻቸውን ያሥተዳድሩ የነበሩ ከ530 በላይ እናቶችን ከዚያ አድካሚ እና አደገኛ የኑሮ ሁኔታ ለማላቀቅ እና የገቢ ምንጫቸውን ለማሻሻል የተቋቋመ ነው።

በአንድ ማዕከል የእንጀራ መጋገሪያ፣ የእህል ወፍጮ፣ የወተት ላሞች እና የሕጻናት ማቆያ አገልግሎቶችን በማቀናጀት እናቶች በተሻለ አካባቢ ሠርተው ገቢ እንዲያገኙ እና ቤተሰቦቻቸውን እንዲደግፉ ዕድል ፈጥሯል።

በተጨማሪም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው እናቶች የቀን ውሎ የሕጻናት ማቆያ እና የምገባ ማዕከል ተጎብኝቷል።

በከተማዋ የቀን ማቆያ አገልግሎትን ለማሥፋፋት የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ሲኾን፣ ለአረጋውያን የምገባ ድጋፍ እና ለተቸገሩ ቤተሰቦች የማኅበራዊ ድጋፍ አገልግሎቶች የሚሰጡባቸው ማዕከላትም በጉብኝቱ ተካትተዋል።

በተለይም የልማት ሥራዎች በዕቅድ ብቻ ሳይገደቡ ወደ ተግባር ሲወርዱ በዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ የሚያመጡትን ተጨባጭ ለውጥ ማረጋገጥ እና ተሞክሮዎቹን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ማስፋፋት የሚጠይቅ መኾኑም ተመላክቷል።

በአጠቃላይ በአዲስ አበባ የተገነቡት እነዚህ ሰው ተኮር የልማት ማዕከላት እናቶችን ከአድካሚ የኑሮ ሁኔታ በማላቀቅ፣ ለሕጻናት የተሻለ እንክብካቤ በማቅረብ እና አረጋውያንን በመደገፍ ማኅበራዊ ፍትሐዊነትን እና አካታች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ መኾናቸው ተጠቁሟል።

✍️ ዘጋቢ: አየለ መስፍን

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

#አዲስ_አበባ #ኅዳር_14_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሩዋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።