5ኛው የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ይካሄዳል፡፡

710

ባሕር ዳር፡ መስከረም 25/2013ዓ.ም (አብመድ) 5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ከእኩለ ቀን በኋላ 8፡00 ይጀምራል።

የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ድንጋጌ መሠረት በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የሚከናወን ይናሆናል፡፡ የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በሚያደርጉት ንግግር ነው የሚከፈተው፡፡ በንግግራቸውም በ2013 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ የሚያከናውናቸው ተግባራትን እንደሚያመላክቱ ይጠበቃል፡፡

Previous articleዓለማቀፉ የልማት ማኅበር ለኢትዮጵያ የ400 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ወሰነ፡፡
Next articleድሮ ቀረ