‎የሉዓላዊነት አዲስ መልክ፦ ከአረንጓዴ አሻራ እስከ ሀገራዊ ህልውና

5

የዘመኑ የሉዓላዊነት ጽንሰ-ሀሳብ ከታሪካዊው የድንበር እና የትጥቅ ጥበቃ ትርጓሜ በተጨማሪ የሀገርን ህልውና እና የዜጎችን ደኅንነት በሚያስቀጥሉ ሁለንተናዊ የህልውና ግንባሮች ላይ የተመሰረተ አዲስ መልክ ይዟል።
‎
‎የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ የዘመኑን ሁለንተናዊ የሉዓላዊነት ጽንሰ-ሀሳብ በተግባር በመተርጎም የሀገርን ህልውና እና የዜጎችን ደኅንነት ከአየር ንብረት ቀውስ እየታደገ ያለ ግዙፍ ሀገራዊ ማሳያ ነው።

በሰፊ የሕዝብ ተሳትፎ የተከናወነው ይህ ስኬት፣ የሀገርን ሥነ-ምኅዳር ከጉዳት በመታደግ እና ዓለም አቀፍ ትብብርን በመሳብ ለአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የአየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ 32) ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ጉልህ ሚና አበርክቷል።
‎
‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሀገር ሉዓላዊነት ከውጭ ወረራ ጥበቃ ባለፈ እንደ አፈር እና ውኃ ያሉ ውድ የተፈጥሮ ሀብቶች በቸልተኝነት እና በተሳሳተ አጠቃቀም ከድንበር ሲወጡ የሚፈጠር የህልውና አደጋ ጭምር ነው።
‎
‎አረንጓዴ አሻራም መሬትን ከማልማት እና የአየር ንብረት ለውጥን ከመጠበቅ ባለፈ የኢትዮጵያን መሬት ከራቁትነት እና ከመሸርሸር በመታደግ የኢኮኖሚ እና የህልውና ሉዓላዊነትን የማስጠበቅ የፊት መስመር ጋሻ ኾኖ አገልግሏል።
‎
‎አፈር ሲሸረሸር እና መሬት ሲራቆት የሀገር ሀብት ወደ ውጭ በድብቅ እየተሰደደ፣ የምግብ ዋስትና እየተናጋ እና የወደፊት ትውልድ ዕጣ ፈንታ እየተበላሸ ይሄዳል፤ ለዚህ ነው መጪውን አደጋ መሠረታዊ በኾኑት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎች መቀልበስ ይገባል የሚባለው።
‎
‎የአረንጓዴ አሻራ የዛሬን ትውልድ ደኅንነት ከማረጋገጥ ባለፈ የነገን ዕንባ የሚጠርግ፣ ሀገራዊ ህልውናን በዘላቂነት የሚያጸና እና ኢትዮጵያን በልማት ጎዳና ከፍ አድርጎ የሚያስቀጥል ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
‎
‎#የመደመር_መንግሥት!
‎
‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
‎
‎#አሚኮ ​#GreenLegacy ​​#SovereigntyRedefined #Ethiopia #COP32
‎
‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_04_2019_ዓ_ም
‎
‎✍️:- በስማቸው አጥናፍ
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየባሕር በር እጦት ኢትዮጵያን በየሦስት ዓመቱ አንድ የሕዳሴ ግድብ የሚያስገነባ ሃብት እያሳጣት ነው።