
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ።
በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ዋዜማ በአንታሊያ ቱርክ በመገኘት ከቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ አጋርነት መሠረት በማድረግ፣ የሁለትዮሽ ትብብራችንን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ ተወያይተናል ነው ያሉት።
COP31ን ለማስተናገድ ለተደረገው ዝግጅት እና ጉባኤው በድምቀትና በስኬት እንዲጠናቀቅ ቱርክዬ እያሳየችው ላለው ጥረት አድናቆቴን ገልጫለሁ ብለዋል።
ይህም ኢትዮጵያ የCOP32 ፕሬዝዳንትነትን ለመረከብ በምታደርገው ዝግጅት ላይ የሚኖረውን አጋርነት እንዲሁም የጋራ ትኩረት በሚሹ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመተባበር የሚያስችሉ ዕድሎችን እንደተመለከቱም ገልጸዋል።
#ኢትዮጵያ #ቱርክዬ #COP31 #COP32 #ዲፕሎማሲ#አንታሊያ
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_01_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
