
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር መክረናል ብለዋል።
በቆይታችንም በዋና ዋና የብሪክስ ቅድመ-አጀንዳዎች እና በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ያለውን ሁለገብ ትብብር የበለጠ በሚያጠናክሩ ሂደቶች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ነው ያሉት።
🇪🇹 🇦🇪
