ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮን አውደ ርዕይ አሥጀመሩ።

3
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልልን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ አውደ ርዕይ አሥጀምረዋል።
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ቢሮው በአውደ ርዕዩ የበለጸጉ እና በሥራ ላይ የሚገኙ ችግር ፈች የኾኑ ሲስተሞችን ለጎብኝዎች ክፍት አድርጓል። ሌሎች ተቋማትም ያለሙትን ሲስተም አስጎብኝተዋል።
“ኤሌክትሮኒክስ ለዲጂታል 2030 መሠረት” በሚል መሪ መልዕክት የዲጂታል መፍትሔዎችን የሚያመላክት የፓናል ውይይትም ተካሂዷል።
በአማራ ክልል በዲጅታላይዜሽን ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እና የተቋማትን የዕድገት ጉዞ አስመልክቶ ውይይት እንደሚደረግም ይጠበቃል።
✍️ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበኢትዮጵያ የመጀመሪያው የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።