
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሰውነት ማጎልበት እና የክብደት ማንሳት ስፖርት የሰውነትን ጥንካሬ ለመጨመር፣ የጡንቻን እድገት ለማፋጠን እና አጠቃላይ የጤና ኹኔታን ለማሻሻል ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የጤና ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
ነገር ግን ስፖርቱ ለውድድር ሲባል ከልክ እና ከአቅም በላይ ሲደረግ ለከፍተኛ የጤና አደጋ ያጋልጣል።
በጣሊያኑ የፓዶቫ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በቅርቡ በ”European Heart Journal” መጽሔት ላይ ጥናት አውጥተዋል። ጥናቱ እንደሚያመለክተው በወንድ የሰውነት ማጎልበት ስፖርተኞች (bodybuilders) ዘንድ በድንገተኛ የልብ ሕመም የመሞት አደጋ እጅግ ከፍተኛ ነው።
በጥናቱ ከተካተቱት ከ20 ሺህ በላይ ወንድ ስፖርተኞች መካከል ከተመዘገቡት ዋና ዋና የጤና አደጋዎች የሚከተሉት ይገኙበታል፦
ጥናቱ እንደሚያሳየው ለልብ ሕመም እና ለጤና አደጋው ምክንያት ተደርገው የተቀመጡ ዋና ዋና መንስኤዎች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው።
#አደገኛ መድኃኒቶችን መጠቀም፦ አናቦሊክ ስቴሮይድ እና ሌሎች የሰውነት ግንባታን የሚያፋጥኑ መድኃኒቶች የልብ ምትን ያዛባሉ። በሂደትም የልብን መዋቅር ያበላሻሉ።
#ከፍተኛ የውኃ እና የምግብ ክልከላ፦ ከውድድር በፊት በፍጥነት ክብደት ለመቀነስ ሲባል የሚደረግ የምግብ ክልከላ እና የሰውነትን ውኃ ማድረቅ ለልብ ሥራ ጎጂ ነው።
#የአእምሮ እና የሥነ ልቦና ጫና፦ ከልብ ሕመም በተጨማሪ 15 በመቶ ያህሉ ሞቶች ከሥነ ልቦና ጫና፣ ከመድኃኒት መጠን ማለፍ እና ከድንገተኛ አደጋዎች ጋር የተያያዙ ናቸው።
#ለስፖርተኞች፦ ሕይወትን አደጋ ላይ ከሚጥሉ አደገኛ መድኃኒቶች መራቅ
#ለሕክምና ባለሙያዎች፦ ስፖርተኞች ውጫዊ ጤንነታቸው ሙሉ ቢመስልም ቅድመ የልብ ምርመራ እና ሕክምና ሊደረግላቸው ይገባል።
#ለፖሊሲ አውጪዎች እና ፌዴሬሽኖች፦ በአደገኛ መድኃኒቶች ላይ ጠንካራ ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋል። እንዲኹም ትምህርት መስጠት እና የስፖርተኞችን ጤና የሚያከታተል አሠራር መዘርጋት ይገባል።
ምንጭ፦ medical brief,escardio.org & athers
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
