
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በነጻ የንግድ ቀጠና ውስጥ ተሰማርተው ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ መፈቀዱን አስመልክቶ ገንዘብ ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል። የመግለጫው ሙሉ መልእክት 👇👇
የሀገራችን የኢንዱስትሪ ልማት በሚፈለገው መጠን እንዳያድግ ምክንያት ከሆኑት መካከል የካፒታል እጥረት፤ የግብአት አቅርቦት ችግር እና የባለሙያ እጥረት በዋንኛነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው። በመሆኑም እነዚህን ችግሮች ደረጃ በደረጃ በማቃለል የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ልማትን ማሳደግ ይገባል።
በዚህም መሰረት ግብአቶች እና ሌሎችም ምርቶች በበቂ መጠን ለገበያ እንዲቀርቡ ለማድረግ አስመጪዎች ምርቱን ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት የሚከፍሉት ቀረጥ እና ታክስ ውስን የሆነውን ካፒታላቸውን በመያዝ ረገድ የሚያሳድረባቸውን ጫና ማቃለል ያስፈልጋል።
በእነዚህ ምክንያቶች አስመጪዎች ግብቶችን እና ምርቶችን ቀረጥ እና ታክስ ሳይከፍሉ ወደአገር አስገብተው ለግብአቱ ወይም ለምርቱ ገበያ ባገኙ ጊዜ ቀረጥ እና ታክሱን የሚከፍሉበትን አሰራር የሚፈቅድ የነጻ የንግድ ቀጠና አሰራር የተዘረጋ ሲሆን፤ ይህንን ስርአት የሚያስፈጸሙ ነጻ የንግድ ቀጠናዎች በየካባቢው የተቋቋሙ መሆኑ ይታወቃል::
እነዚህ ነጻ የንግድ ቀጠናዎች ባለሃብቶችን የበለጠ የሚሰቡ እንዲሆኑ ለማድረግ ከላይ ከተገለጸው በተጨማሪ በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ ተሰማርተው ግብአቶችን እና ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቅዷል።
ሰለዚህ ባለሃብቶች ይህንን እድል በመጠቀም በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ እንዲሰማሩ እናሳሳባለን።
#አሚኮ #ኢትዮጵያ #ኢኮኖሚ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
