
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አካባቢ አንቃሽ በተባለ ቦታ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጽንፈኛው ቡድን አባላት ከነትጥቃቸው ለሰላም መግባታቸውን በቦታው ተገኝተው የተቀበሏቸው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ኮሎኔል አሸናፊ ብርቄ ተናግረዋል።
አባላቱ በተሳሳተ መንገድ ወጥተው ሕዝባቸውን ከመበደል ባሻገር ለአማራ ሕዝብ ያስገኙት ለውጥ አለመኖሩ ዘግይተውም ቢሆን ሲገባቸው መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ሰላም መንገድ መመለሳቸውን ኮሎኔል አሸናፊ ገልጸዋል።
የሰላም አማራጩን ተቀብለው የመጡት ኃይሎች ብሬን እና ክላሽ በመያዝ በቀጣናው ወደተሰማራው ክፍለ ጦር መግባታቸውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል።
ሌሎችም የቡድኑ አባላት ከጥፋት ወጥተው ሕዝባቸውን እና መንግሥትን ይቅርታ በመጠየቅ ወደ ሰላም እንዲመለሱም ኮሎኔሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
