ትንሣኤ የወደቁት የተነሱበት እና ደካሞች የተደገፉበት ዕለት ነው።

10

 

አዲስ አበባ፡ ሚያዝያ 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቤተ መንግሥት ማዕድ አጋርተዋል።

የድጋፉ ተጠቃሚ ግለሰቦች ለተደረገላቸው ግብዣ ምስጋና አቅርበዋል።

“ትንሣኤ” ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በእርሱ ላይ ሥልጣን እንደሌለው ለዓለም ያሳየበት ነው ብለዋል።

“ትንሣኤ የወደቁት የተነሱበት እና ደካሞች የተደገፉበት ዕለት ነውና ኢትዮጵያውያን አቅመ ደካሞችን እና እና የተቸገሩ ወገኖችን አለንላችሁ ማለት እንደሚገባም ገልጸዋል።

መረዳዳት፣ ደስታ እና ሀዘንን በጋራ ማሳለፍ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የኢትዮጵያውያን መልካም እሴታችን በመኾኑ እንዳይጠፋ ልንጠብቀው ይገባልም ብለዋል ግለሰቦቹ።

ሀዘኑም ኾነ ደስታው ያለ ሀገር ትርጉም የለውምና የሀገራችን ሰላም የመጠበቅ የዜግነት ግዴታ አለብን ነው ያሉት የማዕዱ ተጋሪዎች።

ዘጋቢ፦ በለጠ ታረቀኝ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በገዛ ሥልጣኑ ሞትን ድል ነሳ”