ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) ማዕድ አጋሩ።

10

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርተዋል።

በመላው ኢትዮጵያ በክርስትና ጥላ ውስጥ በሚገኙ ቤተ-እምነቶች ያሉ ክርስቲያኖች የትንሳኤን በዓል በተስፋ፣ በመስዋዕትነት እና በአዲስ መነሳት መንፈስ በአንድነት ያከብራሉ። ከሳምንታት የፆም፣ ጥሞና እና ራስን የመመልከት ጊዜ በኋላ ፋሲካ በእውነተኛ አምልኮ፣ መንፈስን አድሶ፣ ቤቶችንም በደስታ ይሞላል። በዘመድ አዝማድ መጠያየቅ እና ማዕድ መካፈልም ፍቅርን ያዳብራል።

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ዓመታዊውን የፋሲካ መዐድ ማጋራት ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በአንድነት ፓርክ በጋራ መታደማቸው ለእውነተኛው የአንድነት መንፈስ ጉልህ ማሳያ ነው።

‎በዓለ ትንሣኤው በመላው ኢትዮጵያ የእምነት፣ ቤተሰባዊነት እና የመታደስ መንፈስ የሚታይበት ጊዜ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ ሁላችንም በዚህ የትንሳኤ መንፈስ ዛሬም፣ ነገም፣ ሰርክ ቤታችንን፣ ልባችንንም ለተቸገሩ ወገኖች እንክፈት ብሏል። በዓሉ መልካም በዓል እንዲኾንም ተመኝቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ትንሣኤያችንንም በትንሣኤው አበሰረ” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
Next article“በገዛ ሥልጣኑ ሞትን ድል ነሳ”