“ካርዳችን ይመራናል ለምንለው አካል ድምጻችንን የምንሰጥበት ነው” የደሴ ከተማ ነዋሪዎች

10

 

ደሴ: ሚያዝያ 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ ይገኛል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዳስታወቀው እስከ ሚያዚያ 1/2018 ዓ.ም ድረስ ከ42 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበዋል።

የምርጫ ምዝገባው በደሴ ከተማ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በሆጤ እና ቧንቧ ውኃ ክፍለ ከተሞች የምርጫ ካርድ ሲያወጡ ያገኘናቸው የደሴ ከተማ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ ማውጣት ከአንድ ዜጋ የሚጠበቅ ነው ብለዋል።

ቅቡልነት ያለውን መንግሥት በመመሥረት ሰላም፣ ልማት እና የሀገርን አንድነት ማስጠበቅ ዋናው መንገድ መኾኑንም ገልጸዋል።

ካርዳችን ይመራናል፤ የአካባቢያችንን የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች ይመልስልናል ላልነው አካል ድምጻችንን የምንሰጥበት ነው ብለዋል።

ምርጫው ሰላማዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅብንን ኀላፊነት እንወጣለን ነው ያሉት።

እያንዳንዳችን የምንሰጠው ድምጽ ትልቅ ዋጋ እንዳለው አስበን የምርጫ ካርድ ማውጫ ጊዜው ሳይጠናቀቅ ካርዳችንን ልንይዝ ይገባል ነው ያሉት። “የካርዳችን ሚና ሀገር የመመሥረት ጉዳይ ነውም” ብለዋል።

1ዘጋቢ፦ መሐመድ በቀለ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleቂምን በፍቅር፤ በደልን በይቅርታ በመሻር ለሀገራችን ልማት፤ ሰላምና አንድነት በጋራ መቆም ይኖርብናል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next article“እኛን ግን የትንሣኤው ጌታ አስተምሮናል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ