
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከቡሩንዲ ቀዳማዊት እመቤት አንጀሊን ንድያይሺሚዬ ጋር ተወያይተዋል።
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የቡሩንዲ ቀዳማዊት እመቤት አንጀሊን ንድያይሺሚዬን ከቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬጋ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተቀብዬ ጉብኝት አድርገናል ብለዋል።
በነበረን ቆይታም በምንሠራቸው ሥራዎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ነበረን ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
