“በዓለ ስቅለትን ስናከብር ከእውነት ጋር በመቆም ይሁን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

6
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። መልእክታቸው እንደሚከተለው ቀርቧል፦
ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት እንኳን አደረሳችሁ።
ዕለቱ የዓለምን በደል ሊሽር፤ የአዳምን ዕዳ ሊክስ መድኃኔዓለም የተሰቀለበት ዕለት ነው። ይህ ቀን መንጋነት ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ የተማርንበትም ነው። ጲላጦስ በኢየሱስ ላይ አንዳች ነገር አላገኘበትም። የተሰበሰበው መንጋ ግን እውነትን መቀበል አልፈለገም። ስለዚህ “ስቀለው፤ አስወግደው ” ብሎ በጅምላ ፈረደ።
በጅምላ ፍርድ የተነሳ እውነት በመረጃና ማስረጃ መወሰኑ ቀርቶ በጩኸት ተወሰነ። ጥቂቶች እውነተኞች ብቻ ከእውነት ጋር ቆሙ። ብዙዎቹ ግን በአፈ ቀላጤዎች ተታልለው ስሜታቸውን ተከተሉ። በዚህ የተነሣ በንጹሕ ላይ ተፈረደ። የሚሞተው ተለቅቆ፣ የማይሞተው ሞተ። ሐሰት ቀን ወጥቶለት፣ እውነት ተሰቀለ።
ይሄንን ቀን ስናከብር ከእውነት ጋር በመቆምና መንጋነትን በመጸየፍ ይሁን።
መልካም በዓል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበዓለ ስቅለት እና ሥርዓቱ
Next articleቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከቡሩንዲ ቀዳማዊት እመቤት አንጀሊን ንድያይሺሚዬ ጋር ተወያዩ።