ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ ጋር ተወያዩ።

7

 

ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ ጋር ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን በይፉዊ የትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

በውይይታቸው ወቅት በተለያዩ ዘርፎች ያሉ ትብብሮችን ለማጠናከር ያለሙ በርካታ የመግባቢያ ሰነዶች ፊርማ አከናውነዋል።

እነዚህ ውይይቶች እና የተፈረሙት ስምምነቶች ለሁለቱም ሀገራት የበለጸገ እና የተባበረ መጻኢ ዕድልን የሚያረጋግጡ፣ የቆዩ ግንኙነቶችንም ወደ ተጨባጭ ትብብር ለመቀየር እንደ ወሳኝ መሠረት የሚያገለግሉ የጋራ ቁርጠኝነታችን ማሳያ ጭምር ናቸው ሲሉ ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

#አሚኮ #ኢትዮጵያ #አዲስአበባ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጤና ተቋማት የነዳጅ እጥረት እንዳይፈጠር ምን እየተሠራ ነው ?
Next articleከጫካ ወደ ሰላም፤ ከጥፋት ወደ ልማት!