አፍሪካ ከውጭ እርዳታ እንድትላቀቅ የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅምን በገንዘብ ማጠናከር ይገባል።

8

 

አዲስ አበባ፡ ሚያዝያ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 39 አባል ሀገራት የተሳተፉበት 16ኛው የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባኤ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል። በዚህ ጉባኤ አፍሪካውያን የአደጋ ስጋት አቅማቸውን ለማስተሳሰር ከመቼውም ጊዜ በላይ በጋራ ሊቆሙ እንደሚገባ አቋም ይዘውበታል።

በዛሬው የጉባኤው ውሎ እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን የ2025 የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባኤ ሪፖርት እና የ2026 የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባኤ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። ውይይት ከተደረገባቸው ጉዳዳዮች መካከልም የአባል ሀገራት ዓመታዊ መዋጮ አንዱ ነው።

የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅምን ለማጠናከር እና አፍሪካ ከውጭ እርዳታ እንድትላቀቅ ይህን ተቋም በገንዘብ ማጠናከር አግባብ መኾኑ ከዚሁ መድረክ ተነስቷል።

በዚህም የአባል ሀገራት ዓመታዊ መዋጮ በመክፈል ተቋሙን እንዲያጠናክሩ መልክት ተላልፏል።

በዚህ ጉባኤ ኢትዮጵያ ለ16ኛው የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ኤጀንሲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር በመኾን ተመርጣለች። የምዕራብ ማፍሪካዋ ሀገር ጊኒ ደግሞ ሊቀመንበር ኾና ትመራለች።

በዚሁ መድረክ ኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ቅነሳ እና ምላሽ፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የግብርና ሥራዎች፣ የሌማት ትሩፋት፣ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅም፣ የምግብ ሉዓላዊነት፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተሞክሮዎቿን ለሌሎች አባል ሀገራት አካፍላለች።

ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ኀይለኢየሱስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ፋይዳ፣ መሶብ እና ኮደርስ የመንግሥት ልዩ ፕሮጀክቶች ናቸው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleበጤና ተቋማት የነዳጅ እጥረት እንዳይፈጠር ምን እየተሠራ ነው ?