“መሶብ፣ ፋይዳ እና ኮደርስ የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ የሚያሳልጡ ናቸው” አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር)

8
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የክልሉን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እና የኢትዮ ኮደርስ አፈጻጸምን እየገመገሙ ነው።
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሥተባባሪ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) መሶብ፤ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እና ኢትዮ ኮደርስ የኢትዮጵያ ትልቅ ፕሮጀክቶች መኾናቸውን ተናግረዋል። የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ የሚያሳልጡ መኾናቸውንም ገልጸዋል።
መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋና ከብልሹ አሠራር የጸዳ እንዲኾን ያስችላል ነው ያሉት። በክልሉ የመሶብ አገልግሎት መስፋፋቱንም አንስተዋል።
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለሁሉም ሥራዎች መሠረት መኾኑንም ገልጸዋል። በክልሉ በርካታ ነዋሪዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ማውጣታቸውንም ተናግረዋል።
ኢትዮ ኮደርስ የሰው ሃብት ልማት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።
ሦስቱን ኢኒሼቲቮች በቅንጅት በመምራት የክልሉን የዲጂታል መሠረተ ልማት የሚያሳልጡ እንዲኾኑ በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው።
Next articleየቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስት ንዴሺሚዬ አዲስ አበባ ገቡ።