የከተማ ኢኮኖሚን ለማነቃቃት በቅንጅት እየተሠራ ነው።

8

 

ባሕር ዳር: መጋቢት 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የከተማ ዘርፍ ተቋማት የ2018 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ገምግመዋል።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሥተባባሪ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) በከተሞች መሠረተ ልማትን በማሟላት የከተማ ኢኮኖሚን ለማነቃቃት በቅንጅት እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል ።

የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኀላፊ አትክልት አሳቤ የኑሮ ውድነት እንዳይባባስ ለማድረግ እና የተመረጡ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሪን የማሳደግ ተግባር እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።

የገበያ ሥርዓት እንዲዘምን በማድረግ የማክሮ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ እየተሠራ መኾኑንም ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኀላፊው የቻለ ይግዛው ተቋማት ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ የአገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል።

የተቋማትን የሳይበር ደኅንነት ለመጠበቅ እየተሠራ መኾኑን ነው የገለጹት።

የአማራ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ አማካሪ ሽቤ ክንዴ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ፣ ጽዱ እና ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ተግባራት እየተሠሩ ነው ብለዋል።

የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለማርካት በማኅበር በማደራጀት የቤት ባለቤት ለማድረግ የቅድመ ዝግጀት ተግባራት መጠናቀቁንም አንስተዋል።

በቤት ግንባታ ዙሪያ የሚስተዋለውን የፋይናንስ ችግር ለመፍታት ከአበዳሪ ተቋማት እና ከባለ ሃብቶች ጋር በቅንጅት እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።

ዘጋቢ፦ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በሰው ሠራሽ አስተውሎት ታግዘው እየሠሩ ነው።
Next article“ምርጫውን ለማደናቀፍ የሚሠሩ ኃይሎችን የጸጥታ ኃይሉ አይታገስም” ኮሚሽነር አስቻለ አላምሬ