
አዲስ አበባ: መጋቢት 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የጤና ሚኒስቴር የ“ዲጅታል 2030” ስትራቴጂን እውን ለማድረግ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሕክምና አገልግሎት እንዲሰጡ እየሠራ መኾኑን አስታውቋል።
ይህ አዲስ አሠራር ባለሙያዎች በእጅ ስልካቸው ወይም በታብሌት በመታገዝ አዳዲስ የበሽታ ምልክቶችን በፍጥነት እንዲለዩ እና ለቀጣይ ሕክምና እንዲልኩ ያግዛቸዋል።
በተጨማሪም በወረቀት ላይ የነበሩ የጤና ፓኬጅ ማንዋሎችን ወደ ሠው ሠራሽ አስተውሎት በመቀየር መረጃን በቀላሉ ለማግኘት ያስችላል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በሙከራ ደረጃ የተጀመረው ይህ ቴክኖሎጂ እያገዛቸው እንደኾነ ሲስተር ፍቅሬ አፋጎ ተናግረዋል።
ቴክኖሎጂው ከርቀት ለሚመጡ ታካሚዎች ፈጣን ውሳኔ ለመስጠት እና ወረቀት በማገላበጥ የሚባክን ጊዜን ለመቆጠብ ረድቷል ነው ያሉት።
በጤና ሚኒስቴር የዲጂታል ጤና ኦፊሰር ገመቺስ መልካሙ እንደገለጹት የታካሚዎችን መረጃ ከወረቀት ንክኪ ነፃ በማድረግ ዲጅታላይዝ ማድረግ የአገልግሎት ጥራትን ለማሳደግ የላቀ ሚና ይጫወታል።
ዘጋቢ፦ ተመሥገን ዳረጎት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
