ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ርእሰ መሥተዳድር ሹመትን አራዘሙ።

14
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ርእሰ መሥተዳድር ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ሹመት ለአንድ ዓመት አራዝመዋል።
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 62(9)እና በዐዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀፅ 2(ለ) መሠረት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አሥተዳደርን በርእሰ መሥተዳደርነት እንዲመሩ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አሥተዳደር
አስመልክቶ በጸደቀው ደንብ ቁጥር 479/2013 አንቀጽ 4(2) እና የዓመቱን የሥራ አፈጻጸም ባቀረቡት መሠረት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሚያዝያ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደን ለአንድ ዓመት ሹመታቸውን ማራዘማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“በትንሣኤ በዓል የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር እየተሠራ ነው” ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ
Next articleበፀሐይ ኃይል ከነዳጅ ጥገኝነት የተላቀቀው አመልድ ኢትዮጵያ