“በትንሣኤ በዓል የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር እየተሠራ ነው” ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ

1
አዲስ አበባ ፡ መጋቢት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኀላፊ ጃንጥራር ዓባይ ኅብረተሰቡ የትንሣኤ በዓልን ያለምንም የዋጋ ጭማሬ እንዲያከብር ለማድረግ የገበያ ማረጋጋት ሥራዎች በስፋት እየተሠሩ መኾናቸውን አስታውቀዋል።
የኢንዱስትሪ ምርቶች፣ የእንስሳት ተዋጽኦ እና የግብርና ምርቶች በኅብረት ሥራ ማኅበራት በኩል በተመጣጣኝ ዋጋ ለኅብረተሰቡ እንዲደርሱ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።
ኀብረተሰቡ የትንሣኤንጰ በዓል ያለምንም የዋጋ ጭማሬ እንዲያከብር የኑሮ ውድነትን በመቀነስ እና ገበያን በማረጋጋት የተሻለ ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።
በበዓሉ የምርት እጥረት እንዳያጋጥም ከክልሎች ጋር በመነጋገር ምርት በበቂ ሁኔታ እንዲገባ ተደርጓል ነው ያሉት።
በከተማ አሥተዳደሩ 240 የሰንበት ገበያዎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል። በሁሉም ማዕከላት ምርቶች በበቂ መጠን ቀርበዋል፤ በዓሉን ምክንያት በማድረግም ከእርድና ከስጋ አቅራቢዎች ጋርም ትስስር ተፈጥሯል ነው ያሉት።
በዓሉን በስኬት ለማክበር እና የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ከጸጥታ አካላት ጋር የተቀናጀ የክትትል እና የቁጥጥር ሥራ እየተከናወነ መኾኑንም አመላክተዋል።
ኅብረተሰቡ በሁሉም የገበያ ማዕከላት በመገኘት የበዓል ገበያ ግዥ መፈጸም እንደሚችል አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ፦ ሰለሞን አሰፌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ልሂድ በወልድያ በአዋጅ መንገሪያው ማክሰኞ ገበያ ሰው መገናኛው”