
ባሕር ዳር: መጋቢት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ክብርት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።
በዲፕሎማሲው መስክ ለሀገራቸው ኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ አስተምህሮ እና ብልህ አመራር ምንጊዜም ይታወሳሉ ነው ያሉት።
ትጉህ እና ከብረት የጠነከሩ ዲፕሎማት ነበሩ ብለዋል በመልዕክታቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
