ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።

3
ባሕር ዳር: መጋቢት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ እና ታላቅ ዐሻራን ማሳረፍ የቻሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።
​አምባሳደር ቆንጂት እስከ ከፍተኛ ዲፕሎማትነት በደረሰ ረጅም የሥራ ዘመናቸው ለሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ያስመዘገቡት ድል እና ያበረከቱት አስተዋጽዖ ሁልጊዜም በክብር የሚታወስ ነው።
​አምባሳደር ቆንጂት ለኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ከነበራቸው አበርክቶ ባለፈ ለሴት ዲፕሎማቶችም የጽናት እና የጥንካሬ ተምሳሌት ነበሩ ነው ያሉት።
​ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleሁለተኛው የኢትዮጵያ እና ብሩንዲ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ሥብሠባ እየተካሄደ ነው።
Next articleፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።