
ባሕር ዳር: መጋቢት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ እና በብሩንዲ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የሁለተኛው የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ሥብሠባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ሥብሠባው በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ መከላከያ እና የጥታ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ስምምነቶችን ለመፈጸም እና አዳዲስ የትብብር መስኮችን ለመለየት ያለመ ነው ተብሏል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አምባሳደር ዘሪሁን አበበ ሥብሠባው የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ እና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማስፋት ያግዛል ብለዋል ።
በአቪዬሽን ፣በግብርና ፣መሠረተ ልማት፣ በኀይል እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት የሚደረገው ይህ ሥብሠባ ይበልጥ ሁለቱ ሀገራትን የትብብር መስክ እንደሚያሳድገው ገልጸዋል።
የቡሩንዲ የውጭ ጉዳይ፣ ክልላዊ ውህደት እና የልማት ትብብር ሚኒስቴር የሁለትዮሽ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄኔራል እና የብሩንዲ ልዑክ መሪ አምባሳደር ኤጊድ ንዲኩሪዮ ይህ ሥብሠባ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት ይበልጥ ለማላቅ ይበጃል ብለዋል።
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሁለተኛው የኢትዮ ብሩንዲ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ሥብሠባ በሁለቱ ሀገራት የተወከሉ ከፍተኛ ባለሙያዎች በቀረቡ ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
