ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።

8
ባሕር ዳር: መጋቢት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል።
አምባሳደር ቆንጂት ከልጅነት እስከ ዕውቀት ኢትዮጵያን በዲፕሎማትነት በማገልገል፣ ከአምባሳደር ዮዲት እምሩ ቀጥለው ሁለተኛዋ ሴት የኢትዮጵያ አምባሳደር ናቸው። ለሕግ፣ ለአሠራር፣ ለፕሮቶኮል እና ለኢትዮጵያ ጥቅሞች በነበራቸው የጸና አቋም እናስታውሳቸዋለን ነው ያሉት።
ከእርሳቸው በኋላ አያሌ ሴት ዲፕሎማቶች በመስኩ እንዲሠማሩ መንገዱን ማስፋታቸውን ገልጿል።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያውያን መጽናናት እመኛለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleለጥንቃቄ! የበልግ ወቅትን ተከትሎ ሊከሠቱ የሚችሉ 10 የጤና ሥጋቶች።
Next articleሁለተኛው የኢትዮጵያ እና ብሩንዲ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ሥብሠባ እየተካሄደ ነው።