“የቀይ ባሕር አሥተዳደርን አካታች በማድረግ ዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሳለጥ ይገባል” የኢትዮጵያ የባሕር ኃይል አዛዥ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ

12
አዲስ አበባ፡ መጋቢት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 4ኛው የቀይ ባሕር እና የገልፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በጉባኤው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የባሕር ኃይል አዛዥ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ የቀይ ባሕር አሥተዳደር አካታች መኾን አለበት ብለዋል።
አካታች ይሁን ሲባል የባሕር ተጋሪዎች የባሕር በሩ ዝግ ሀገራት እና የአካባቢው ሌሎች ማኅበረሰቦችም ማለት እንደኾነ ጠቁመዋል።
የቀይ ባሕር አሥተዳደር አካታች እና አግባብነት ያለው ሲኾን የዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት የተሳለጠ እና የተሰናሰለ አንዲኾን ያስችላል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ከራሷ ባለፈ የቀጣናውን ሰላም እና ደኅንነት በማረጋገጥ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ ሽብርተኝነትን እና የባሕር ላይ ዝርፊያን ለመከላከል ወሳኝ መኾኑንም አስረድተዋል።
የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ባዘጋጀው በዚህ ኮንፈረንስ አጥኝዎች፣ ፖሊሲ አውጭዎች እና የቀጣናው ሀገራት ተወካዮች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፦ ዓንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየለውጥ ዓመታቱ ስኬት በሐረሪ ክልል
Next articleለጥንቃቄ! የበልግ ወቅትን ተከትሎ ሊከሠቱ የሚችሉ 10 የጤና ሥጋቶች።