አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

8
ባሕር ዳር: መጋቢት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ)አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
አምባሳደር ቆንጂት የውጭ ጉዳይ ሚንስቴርን በ1950ዎቹ በለጋ እድሜያቸው እንደተቀላቀሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። አምባሳደሯ ከዴስክ ኦፊሰርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት አገልግለዋል።
አምባሳደር ቆንጂት ከዮዲት እምሩ በመቀጠል በኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሴት አምባሳደርም ናቸው።
አምባሳደሯ በኦቶዋ፣ ካይሮ፣ ቴል አቪቭ እና ቬይና በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ኾነው አገልግለዋል።
በአፍሪካ ኅብረት እና በተባባሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንም ቋሚ መልዕክተኛ በመኾን ሠርተዋል።
ከሰኔ 2009 እስከ መስከረም 2011ዓ.ም ደግሞ ኢጋድ በመራው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ላይም ልዩ አማካሪ ነበሩ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአምባሳደር ቆንጂት ሕልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
Next articleየሕማማት ሳምንትን ከመከራ መታሰቢያነት ባለፈ የርህራሄ ማድረግ ይገባል።